አዲስ የተሳቢና የጭነት አካላት ምርት በገበያ ላይ ዋለ

ድርጅቱ ቀደም ብሎ ያመርታቸው ከነበሩትና በጥራት ደረጃቸው ታዋቂ ከሆኑት ምርቶቹ በተጨማሪ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሳቢና የጭነት አካላት ዲዛይን በማድረግ አምርቶ መሸጥ መጀመሩን ሲገልፅ በደስታ ነው፡፡

ተሳቢዎቻችንና የጭነት አካላት ዓለም አቀፍ ደረጃን አሟልተው ዲዛይን የተደረጉና የተፈበረኩ ስለሆነ ከማንኛውም ስጋት ነፃ ናቸው፡፡

የቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካን የተሳቢና የጭነት ተሸከርካሪዎች አካላት ምርቶች ልዩ የሚያደርጋቸው፡-

  • አከስልና ሰስፔንሽናቸው በጥንካሬውና አስተማማኝነቱ የታወቀውና ለከባድ ሥራ የሚያገለግለው BPW TRIDEM ሲሆኑ የተመረቱትም 3*12 ቶን የመሸከም አቅም ካለው አራት ማዕዘን ቱቦ መሆኑና አካሉም የጀርመን ስሪት መሆኑ፣
  • ፍሬኑ (Brake System) የተሠራው ከዝነኛው WABCO ብራንድ መሆኑ፣
  • ምርቶቹ በአንድ እጅ ዝገት መከላከያና በሁለት እጅ ኒትሮ የተቀቡ መሆኑ፣
  • የመጨረሻው ቀለም በደንበኞች ምርጫ መወሰኑ፣
  • ምርቶቹን በአጭር ቀጠሮ ለደንበኞች ማቅረብ መቻሉ እና
  • ከሽያጭ በኋላ ያለው አስተማማኝ አገልግሎቱ ናቸው፡፡